Wednesday, 18 May 2016

በኢቲቪ ስተላለፍ የነበረው የ AXE DODORANT ማስታወቂያ

     
   ይህ SPRAY MORE AND GET MORE ኣንድ ወንድ የAXE ዶዶራንትን ሲጠቀም በኣጭር ሰኣት ሁለት ሴቶችህ መወነን አንደሚችል ተደርጎ ሲተለልፍ  የነበረ ማሰታወቂያ ነው ። በቪዲዮ ለመታየት የተጠቀማቻው የሴቶች ብዛተ ሁለት መሆኑም  SPRAY MORE GET MORE የሚል የእንግሊዘኛ መፈክሩ ሲተረጎም ግን ብዙ በተጠቀመበት ብዙ ሴቶች መወነን አንደሚችሉ ነው የምያስተላልፈው።


  የኢትዮጵያ ፋዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስለ ማሰታወቂያው ያወጣው ኣዋጅ ህግ ቁጥር 759/2012 ገፅ 6520 ክፍል ሶስት ለማሰታወቅያ በጠቅላላው ይዘትና ኣቀራረብ ሲገልፅ ማንኛውም ማስታወቂያ ማንኛውም ህግ መልካም ሰነ ምግባር የማይፃረር ተገቢ ሰለሆነ ኣገላለፁ ነፃ የሆነ ማህበረሰቡ ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች የሚያሰከብርና የሸማቹን ህጋዊ ጥቅም የማይጎዳ መሆን ኣለበት ይላል ።

  ሆኖም ግን ይህ ማስታወቅያ አነዚህ ህጎች ግምት ውስጥ ኣላሰገባም።በዚህ ማስታወቂያ የሚታዩ ስህተቶች ስገመግም በ ኣንደኛ ደረጃ የምታየኘ ክፍተት የ ሴቶችን ስብእና ወይም ክብር መጋፈቱን ነው ። ኣብዛኛዎቹን የ ኣለማችን ማስታወቅያዎች በ ሴቶች ይተዋወቃሉ። የዚህ ማስታወቂያ ግን በ ኣንድ የዶዶራንት ኢቃ ብዙ ሴቶችን መግዛት ማለትም ሙሉ በ ሙሉ የ ሴቶች ስብእና ኣለመቀበል ወይም ሴቶች ያላቻው ኣስተሳሰብ በጣም የወረደና በ ቀላሉ ወደፈለግንባቸው መውሰድ ኢንደምንችል ነው የምያሳየው
  በተጨማሪም ይህ ማስታወቅያ ከማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ኣንፃር ስታይ የ ሃገራችን የ ሃይማኖትና የ ማህበረሰብ ህግ ማንቋሸሽና መቃረኑን በ ግልፅ ይታያል። ስለዚህ ይህ AXE DODORANT ማስታወቅያ ብዙም በህላችን ስያንቋሽሽ ማህበረሰቡን እንዲረዳን ዘንድ እና እንድጠቀም ዘንድ ይህ ማስታወቅያ ብልግና እንድሁም በህላችን በማይረሳ መልኩ ብተዋወቅ በህብረተሰባችን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ይኖረዋል ብዬ ኣምናለሁ።


  በኣጠቃላይ ይህ AXE DODORANT ማስታወቅያ ስንመለከት ማለትም በ ማህበረሰብ ዘንድ ምንም ኣይነት መልእክት ያስተላልፋል ወይም እንዴትስ መረዳት ይችላሉ። ምክንያቱንም ማስታወቅያውን ስንመለከት AXE DODORANT            ኣንድ ሰው ተጠቅሞ ሁለት ሴቶች ማማለል እንደምችል ተመልክተናል። ነገር ግን ይህ ማስታወቅያ ባህላችንን ፣ ሃይማኖታችንን ፣ እንድሁም ህጋችንን የምፃረር ስለሆነ ይህ ማስታዋቅያ ለ ወደፊቱ በተሻለ መልክና እንድሁም ማህበረሰባችን በማያሳፈር መልኩ ብሰራ እንደኔ እንደኔ መልካም ነው ብዬ ኣስባለሁ።

No comments:

Post a Comment