Monday, 9 May 2016

የመቀለ ከተማ ማስታቅያ ሰሪዎች እነማን ናቸው

                             

በዚህ ሳምንተ በመቀለ ከተማ ለሚሰሩ ማስታወቅያዎች  ለማየተና አሰራራቸው ለመገምገም በሁሉም የውጭ ማስታወቅያ (OUT DOOR ADVERTING)በሚበዛባቸው አከባቢ ተዘውሬ አይቸለሁ ሆነም ግን ሁሉም የውጥጥ ማስታወቅዎች ማለት ባነር ቢቦርድና ሌሎች ፖስተሮች ስመለከት አንዳቸውም እንኳን ከመንቀፍ የሚድኑ አልነበሩም።

በዚህ ሳዓት ሊገመገሙ የሚችሉ የውጭ ማስታወቅያዎች ገምገሜ በፎቶ ለማስደገፍ ይÏት የሄድኩት የሚገመገም ማስታወቀያ ከመብዛት የተነሳ በፎቶ ሞልታለች።ምክያቱም ሁሉም ማስታወቅያዎች ከግምገማ አያመልጡም ነበርና ሞባይሌ ከሞላ በውሃላ ዝም ብየ ወደ ግቢየን ተመለስኩ።በዛ ሳዓት ማስታወቅያዎችሁ በትክክል ካለመስራታቸው አላናደደኝም።ይልቅስ እኛ የህዝብ ግኑኝነት ተማሬዎች ከተመርቅን በውሃላ ሞያው በሚጠይቀው መልኩ ስለምንሰራ ማስታወቅያ የሚያሰሩ ሰዎች እነዚህ በልምድ የሚሰሩ ማስታወቅያ ሰሪዎች በመተው ወደኛ ሊመጡ ይችላሉና ከፍተኛገቢና ስራ እናገኛለን የሚለ ተስፋ ነው ያደረኝ።



ሆነም ግን እንድ ጥያቄ አለኝ ለሞኑ የመቀለ ከተማ ማስታወቅያዎች ማን ነው የሚሰራቸው ? በእርግጥ በእገራችን በማስቅያ ስራ ሞያ የተመረቀ የለም ሁሉም ማስታወቅያ ሰሪዎች በልምድ ነው የሚሰሩ። ግን የመቀለ ማስታወቅ ሰሪዎች ምንም እንኳን በልምድ ቢሰሩም ቢንስ ግን የተወሰኑ የማስታወቅያ ህገ ናደንብ ወይም አሰራራ ግምት ውስጥ አስገብው መስራት አለባቸው። ምክንያቱም አንድ ለጥሩ ብሎው የሚሰሩትን ምስል ፣ቋንቋ ወይም መሪ ቃል ለሚሰራላቸው ድርጅቶች ወደልተፈለገ የህዝብ ጥላቻ ወይም ትርፈ ቢስ ልያደረጋቸው ይችላል።

No comments:

Post a Comment